image
image
image
image
image

የመልካም አስተዳደር ቅ/አ/ጽ/ቤት በአዲሱ የቅንጅታዊ አሠራር ማስፈፀሚያ መሠረት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክላስተሮች ዕውቅና ሰጠ።

የካቲት 4, 2017
የምዘናውን ሪፖርት ያቀረቡት የቅንጅታዊ አሠራር ቡድን መሪ አቶ ሀይማኖት ጌራወርቅ በክላስተራቸው የታዩትን ጠንካራና መስተካከል ያለባቸውን አበይት ጉዳዮን ዘርዘር አዶርገው አቅርበዋል። የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ይልማ ተረፈ እንዳሉት ክላስተሮች ተቀራራቢ ቁመና እንዲኖራቸው የሚሰጠው እውቅና የተሻለ ተነሳሽነት አለው በማለት ሁሉም ክላስተር በተቀናጀበት ተግባር ውጤታማ ለመሆን የተሰጠውን ሀላፊነት ሊወጣ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የክላስተር አስተባባሪዎችና ቴክኒክ ኮሚቴዎች በያዙት እቅድ መሠረት ትኩረት ሰጥተው በመስራት ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ይልማ ተረፈ አያይዘው በቅንጅት ተሰርቶ የመጣውን ውጤት የላቀ እንዲሆን ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። ክ/ከተማውን ተወዳዳሪና ተፍካካሪ ማድረግ ውጤት ማስመዝገብ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም ከአገልግሎት አሠጣጥ ቅልጥፍና ጋር በማጣመር ውጤት ማምጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል። ቅንጅታዊ አሠራሩ ውጤት ማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ተሻጋሪ ተግባራትን በመስራት የሚታይ ውጤት ማምጣት ይገባል ብለዋል። በክላስተር የተደራጁት 7ቱንም ክላስተር ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በዚሁ አደረጃጀትና አፈፃፀም የክላስተሮችን አቅም ለመገንባት በሚያስችል መልኩ መመዘን ደረጃ ማውጣት እውቅና ሰጥተናል ሲሉ ገልፀዋል። የክላስተር አስተባባሪዎች የተሰጠው እውቅናና ሽልማት ለቀጣይ የተሻለ መነሳሳት ይፈጥራል ሲሉ አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ