Welcome to Lideta Subcity Good Governance, Compliance and Grievance Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጡ ፍትሃዊነትን ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይተጋል!

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት


የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና ለሚያጋጥም ቅሬታና አቤቱታ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት፣ ስህተቶችን ለማረምና አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ፤ በየደረጃው ያለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊ እና ሠራተኛ ለህብረተሰቡ በሚሰጡት አገልግሎት አስተዳደራዊ ጥፋትና በደል እንዳይፈፀሙ መከላከልና ተፈጽሞ ሲገኝ ተጠያቂ ለማድረግ እና በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ የመስሪያ ቤት ኃላፊና ሠራተኛ በማፍራት ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡

አላማውን መሰረት በማድረግ በክፍለ ከተማችን በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር እና የአገልግሎት ፍላጎት በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶችና ብዛት እንዲጨምር በማድረጉ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ከነዋሪው ሕዝብ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም በየጊዜው አዳዲስ ማሻሻያዎች እየተደረገ ይገኛል፡፡ ... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ይልማ ተረፈ , የልደታ መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

ዋና ዋና አገልግሎቶች

የቅሬታና አቤቱታ ምርመራ አገልግሎት
የወሳኔ አፈጻጸም ክትትል አገልግሎት
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መለየትና መፍታት፤ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርና ድጋፍ አገልግሎት
ዜና | Oduu | News
የከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ምልከታ አደረገ ።

በምልከታው ወቅት ምክር ቤቱ በክፍለ ከተማው የሚገኝው የአንድ ማዕከል አገልግሎትና ሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በጎብኘት ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ሂደት፣ ፍጥነት እና ጥራት ተመልክቷል። የምክር ቤቱ አባላት ለሕዝብ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚደረጉ ጥረቶችን በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነትንና ውጤታማነትን የበለጠ ለማሻሻል የተሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል። የልደታ ክፍለ ከተማ በአንድ ማዕከል አገልግሎትና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አማካኝነት የተገልጋዮችን ጥያቄና ፍላጎት በማዳመጥ ፈጣንና ቀልጣፋ ምላሽ እየሰጠ ነው በክፍለ ከተማው የተለያዩ አገልግሎቶችን ፈልገው የሚመጡ ተገልጋዮች በአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽ በሆነ ሁኔታ ጉዳያቸውን በማስፈጸም አገልግሎታቸውን አግኝተው እየተመለሱ መሆኑን ተገልፀዋል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ የአገልግሎት አሰጣጡ ፈጣን እና ችግር ፈች እየሆነ ነው ሲሉ ተገልጋዮች ገለፁ

በአስተዳደሩ በተቀናጀ የአንድ ማዕከል እና በተቋማት የሚሰጠው አገልግሎት ውጤታማ መሆኑንም ተገልጋዮች ገልፀዋል። በአስተዳደሩ አገልግሎት ፈልገው የመጡ ነዋሪዎች እንደተናገሩት በልደታ ክ/ከተማ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ምልልስን የቀነሰ እና ችግር ፈች እየሆነ ነው ብለው ይህ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ገልፀዋል። የአገልግሎት አሰጣጡ ተደራሸና የህብረተሰቡን ፍላጎት ያማከለ እየሆነ በመምጣቱ እጅግ ደስተኞች ነን ብለዋል ተገልጋዮች።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ "የልደታ AI አምባሳደሮች" በሚል መሪ ቃል ከየተቋማት ለተውጣጡ የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ስልጠና መስጠት ተጀመረ

በስልጠና ማስጀመሪያው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት አገልግሎት አሰጣጡን በዲጅታል ቴክኖሎጅ በማገዝ የህዝብን እንግልት ለመቀነስ እና የስማርቲ ሲቲ ግንባታን እቅድን ለማሳካት በትኩረት እየሰራን ነው ብለው በዛሬው ዕለት ለተቋማት ሰራተኞች መሰጠት የጀመረው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ተግባሩን በማገዝ ረገድ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል በማለት ገልፀዋል። የተጀመረውን "የዲጂታል ኢትዮጲያ 2030 "ስትራቴጅን ስኬታማ ለማድረግ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል። የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋይ እርካታን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ መሰል ስልጠናዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ገልፀዋል ወ/ሮ ልዕልቲ። ሰላምና ደህንንነት ከማስጠበቅ አንፃርም AI ያለው ፋይዳ የላቀ እንደሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል። ስልጠናው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን ሰልጣኝ አምባሳደሮች ከስልጠናው በኋላ በየተቋማቸው AIን የሚጠቀሙና አገልግሎቱ የላቀ እንዲሆን የሚያግዙ ይሆናል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ። ሰው ሰራሽ አስተውልዎ (AI) አሰልቺና ረጅም የሆኑ ቢሮክራሲያዊ ሂደቶችን በማቃለል፣ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በፍጥነትና በጥራት ለመመለስ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በመድረኩ ተገልጿል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
የመልካም አስተዳደር ቅ/አ/ጽ/ቤት በአዲሱ የቅንጅታዊ አሠራር ማስፈፀሚያ መሠረት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክላስተሮች ዕውቅና ሰጠ።

የምዘናውን ሪፖርት ያቀረቡት የቅንጅታዊ አሠራር ቡድን መሪ አቶ ሀይማኖት ጌራወርቅ በክላስተራቸው የታዩትን ጠንካራና መስተካከል ያለባቸውን አበይት ጉዳዮን ዘርዘር አዶርገው አቅርበዋል። የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ይልማ ተረፈ እንዳሉት ክላስተሮች ተቀራራቢ ቁመና እንዲኖራቸው የሚሰጠው እውቅና የተሻለ ተነሳሽነት አለው በማለት ሁሉም ክላስተር በተቀናጀበት ተግባር ውጤታማ ለመሆን የተሰጠውን ሀላፊነት ሊወጣ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የክላስተር አስተባባሪዎችና ቴክኒክ ኮሚቴዎች በያዙት እቅድ መሠረት ትኩረት ሰጥተው በመስራት ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ይልማ ተረፈ አያይዘው በቅንጅት ተሰርቶ የመጣውን ውጤት የላቀ እንዲሆን ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። ክ/ከተማውን ተወዳዳሪና ተፍካካሪ ማድረግ ውጤት ማስመዝገብ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም ከአገልግሎት አሠጣጥ ቅልጥፍና ጋር በማጣመር ውጤት ማምጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል። ቅንጅታዊ አሠራሩ ውጤት ማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ተሻጋሪ ተግባራትን በመስራት የሚታይ ውጤት ማምጣት ይገባል ብለዋል። በክላስተር የተደራጁት 7ቱንም ክላስተር ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በዚሁ አደረጃጀትና አፈፃፀም የክላስተሮችን አቅም ለመገንባት በሚያስችል መልኩ መመዘን ደረጃ ማውጣት እውቅና ሰጥተናል ሲሉ ገልፀዋል። የክላስተር አስተባባሪዎች የተሰጠው እውቅናና ሽልማት ለቀጣይ የተሻለ መነሳሳት ይፈጥራል ሲሉ አንስተዋል።

image
image
image

የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች

በልደታ ክ/ከተማ የመልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር ፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡