image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ "የልደታ AI አምባሳደሮች" በሚል መሪ ቃል ከየተቋማት ለተውጣጡ የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ስልጠና መስጠት ተጀመረ

የካቲት 1, 2017
በስልጠና ማስጀመሪያው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት አገልግሎት አሰጣጡን በዲጅታል ቴክኖሎጅ በማገዝ የህዝብን እንግልት ለመቀነስ እና የስማርቲ ሲቲ ግንባታን እቅድን ለማሳካት በትኩረት እየሰራን ነው ብለው በዛሬው ዕለት ለተቋማት ሰራተኞች መሰጠት የጀመረው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ተግባሩን በማገዝ ረገድ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል በማለት ገልፀዋል። የተጀመረውን "የዲጂታል ኢትዮጲያ 2030 "ስትራቴጅን ስኬታማ ለማድረግ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል። የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋይ እርካታን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ መሰል ስልጠናዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ገልፀዋል ወ/ሮ ልዕልቲ። ሰላምና ደህንንነት ከማስጠበቅ አንፃርም AI ያለው ፋይዳ የላቀ እንደሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል። ስልጠናው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን ሰልጣኝ አምባሳደሮች ከስልጠናው በኋላ በየተቋማቸው AIን የሚጠቀሙና አገልግሎቱ የላቀ እንዲሆን የሚያግዙ ይሆናል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ። ሰው ሰራሽ አስተውልዎ (AI) አሰልቺና ረጅም የሆኑ ቢሮክራሲያዊ ሂደቶችን በማቃለል፣ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በፍጥነትና በጥራት ለመመለስ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በመድረኩ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ