image
image
image
image
image

የአንድ ማዕከል አገልግሎት በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ነሀሴ 21, 2017
አስተዳደሩ የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በአንድ ማእከል አገልግሎት ነዋሪውን እያገለገለ ይገኛል። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ረቡዕና ዓርብን ማዕከል አድርጎ የተገልጋዮችን ቅሬታ ለመቀነስ የልደታ ክፍለ የቅሬታ እና አቤቱታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ፥የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ተስፋዬን ጨምሮ የዋና ስራ አስፈፃሚዎች አማካሪዎች በተገኙበት እየተሰጠ ሲሆን የበርካቶች ችግር እየተፈታ እንደሚገኝ የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን በቦታው ተገኝቶ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች ገልፀዋል። በአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጡም የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ በቂ ምላሽ ያላገኙ ነዋሪዎች ምላሽ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በአንድ ማእከል አገልግሎቱ አንድ ዓይነት ጉዳይ ያላቸውን በጋራ ምላሽ በመስጠት፣ ወረፋን በመጠበቅ የሚጠፋ ጊዜን በመቆጠብ፣ ብልሹ አሰራርን ለማስወገድና ግልፀኝነትን ለመፍጠር ፣ እንዲሁም በቢሮ ያልተገደበ አገልግሎት በመስጠት አንዱ ለአንዱ ምስክር የሚሆንበትን አሰራርም በመፍጠር የተገልጋዩን ህብረተሰብ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ለመመለስ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች