image
image
image
image
image

አዲስ አበባ የበለፀገች የለመለመች በማድረግና ፍትሀዊ የሆነ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

ህዳር 9, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን ተሳትፎ ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ወሆኑ ተገለፀ። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በመድረኩ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማውና በወረዳዎች በራስ አቅም የማህበረሰብ አቀፍ ዴኬር በመስራት ልጃቸውን በተመጣጣኝ የሆነ ምግብና ምቹ አካባቢ በመፍጠር ልጆቻቸው በመያዝ እናቶች ልጆቻቸውን በማስቀመጥ ስራ ሰርተው የተሻለ ገቢ እንዲኖራቸው ለማድረግ ተችሏል። በተለያዩ አካባቢዎች የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች በመገንባታ ህፃናት እንዲቦርቁና እንዲጫወቱ ለማድረግ በርካታ ስራዎች በክፍለ ከተማው ተሰርቷል ብለዋል ለወጣትች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በመገንባታ ወጣቱ በስነ ምግባር እንዲታነፅ ስፖርት በመስራት ንቁና ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ሀይል እንዲሆን በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ገልፀዋል ወ/ሮ ልዕልቲ አያይዘው እኛ በኛ ይህን ሰርተናል የጎደሉ ነገሮችን በጋራ በመስራት የልደታ ከፍታን ማረጋገጥ ይገባል በማለት ገልፀዋል። ክፍለ ከተማው የፀጥታ ችግር መለየት በጋራ መስራት ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘው የብልሹ አሰራርና ሌብነትን አብረን መታገል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች