image
image
image
image
image

"በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" የልደታ ክፍለ ከተማ መልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት የስራ ተሞክሮ እና ልምዱን አካፈለ።

ታህሳስ 15, 2017
በልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ ያደረገው የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አቻ ጽ/ቤት ሲሆን የጽ/ቤቱ ሀላፊ እና ባለሞያዎች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል። የልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይልማ ተረፈ በልምድ ልውውጡ ላይ እንዳሉት በክ/ከተማው የመልካም አስተዳደር ስራዎች ጉዳይ እንደተቋም ተቀናጅቶ የመፍታት ችግር እንደነበር አስታውሰው በአዲስ መልክ የተዋቀረው የክ/ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ በሰጠው ልዩ ትኩረት ጽ/ቤቱ በተሻለ የአፈፃፀም ቁመና ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። አቶ ይልማ አያይዘው የአመራሩን የተግባር ስምሪት በማስተካከል፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ተቋማዊ እንዲሆን በማስቻል እና ህብረተሰቡን የጉዳዩ ባለቤት በማድረግ በእቅድ የሚመራ የመልካም አስተዳደር ችግር አፈታት ተግባር ተጨባጭ ውጤት ማምጣት ተችሏል ሲሉ ለአቻ ክ/ከተማ ጽ/ቤቱ ልምዳቸውን አካፍለዋል። በቅሬታና አቤቱታ በኩል በየተቋሙና ወረዳዎች የተደራጀውን የቅሬታ ኮሚቴ ከመከታተልና መደገፍ ባሻገር ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለማዳመጥ የህብረተሰቡ ጋር መድረኮችን በማዘጋጀት አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያዳምጥና የቅሬታውን አግባብነት አይቶ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለውጥ እንደመጣበት አቶ ይልማ አክለው ገለፃ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ በማድረግ በአገልግሎት ቀን ተገልጋዮችን ግልፅ በሆነ አግባብ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት በተገኙበት አገልግሎት ፍትሃዊና የተገልጋይን እርካታ በሚጨምር መልኩ መሰጠቱ ለውጤቱ አበርክቶ እንዳለው ተነስቷል። በልምድ ልውውጡ ላይ ተካፋይ የሆኑት የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ እና ባለሞያዎች እንደገለፁት ከአቀባበል ጀምሮ ለተሰጣቸው ቅንነት የተሞላበት ገለፃ አመስግነው ከክ/ከተማው ያገኙት ልምድ ለቀጣይ ስራቸው እንደ ግብዓት እንደሚጠቀሙበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች