image
image
image
image
image

የህብረተሰቡን መሠረታዊ ችግሮች ለይቶ ለመፍታት ርብርብ እንደሚደረግ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ነሀሴ 29, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባላት የህብረተሰቡ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው ተብለው ከክ/ከተማ እስከ ብሎክ በተለዩ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል። እነዚህ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሙሉ በመሉ ሲፈቱ የክ/ከተማው ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እቅዱ ያመላክታል። የካቢኔ አባሉቱ ውይይት ከህብረተሰቡ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄ የተሰጠበትን አግባብ በመገምገም ለቀጣይ ተግባር አቅጣጫ ማስቀመጥ አላማ ያደረገ ነው። የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን በማስፈን፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሃዊ፣ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ተልዕኮው የሆነው ክ/ከተማው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ወደ ተግባር ተገብቷል። ውይይቱን የመሩት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ዓመት ማህበረሰቡ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ እየፈታን እንሄዳለን፤ በበጀት ዓመቱ የማህበረሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስራዎችንም እናከናውናለን ሲሉ ገልፀዋል። ማህበረሰቡ በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚኖረውን ተሳትፎ በተደራጀ መንገድ በመምራት ችግሮችን በዘላቂነት መቅረፍ ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ልዕልቲ ለህዝብ ተጠቃሚነት ያለመታከት ሌት ከቀን እንሰራለንም ብለዋል። አቶ አራርሳ ድሪባ የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስ በየደረጃው ያለ አመራር የመሪነት ሚናውን በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል። የህዝብ ጥያቄዎችን በተቀናጀ መንገድ እየመለስን መሄድ ይኖርብናል ያሉት አቶ አራርሳ በምንሰራቸው ተግባራት ሁሉ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል። የሌብነት አስተሳሰብና ተግባርን በተጀመረው አግባብ እየታገሉ የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባም ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች