image
image
image
image
image

"አስተዳሩ ጠንካራና ዘላቂ የሆነ ተቋም በመገንባት ተደራሽ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እየሰጠ ነው" ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

ህዳር 18, 2017
"እየተሰጠ ያለው ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት አስተዳደሩ ለተቋም ግንባታ የሰጠውን ትኩረት ያሳየ ነው" ተገልጋዮች በልደታ ክ/ከተማ እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የማህበረሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለመመለስ አስችሎናል ብለዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለውም ጠንካራና ዘላቂ ተቋም እየገነባን ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት እየሰጠን ነው ያሉ ሲሆን በዚህም የማህበረሰቡን ዕርካታ እያረጋገጥን እንገኛለን በማለት ገልፀዋል። በአስተዳደሩ በየትኛውም ተቋም የሚሰጡ አገልግሎቶች እንግልትን የሚቀንሱ እና በአፈፃፀማቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እየሰራን ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በምንሰጠው አገልግሎት እርካታ እንዲረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል። አገልግሎት አሰጣጣችን ለማህበረሰቡ አዳጊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ በትኩረት ሰርተናል ብለዋል ወ/ሮ ልዕልቲ ። ከዚህ በፊት በተገልጋዩ ዘንድ ምሬት ይፈጥሩ የነበሩ አሰራሮችን እየፈተሽን የማረም ስራ እያከናወን ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በተገልጋይ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በየደረጃው እየሰራን ነው ሲሉ ገልፀዋል። ተገልጋዮች በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት እያገኘን ነው ብለው ይህም አስተዳደሩ ለተቋም ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ያሳየ ነው በማለት ተናግረዋል። ተገልጋዮች አክለውም በተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ችግራችን ይደመጣል ለችግራችንም ፈጣን እና ተገቢ ምላሽ ይሰጠናል ብለው ለዚህም አስተዳደሩን እናመሰግናለን ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች