image
image
image
image
image

ውጤታማ ተቋማዊ ቅንጅት የጋራ ግቦችን ለማሳካት እና ውጤታማ የሀብት አጠቃቀምን ለማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

ጥቅምት 16, 2017
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት 'የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ማስፈፀሚያ' ማንዋል ላይ ውይይት ተደረገ። በውይይት መድረኩ ላይ የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንዳሉት ውጤታማ ተቋማዊ ቅንጅት የጋራ ግቦችን ለማሳካት እና ውጤታማ የሀብት አጠቃቀምን ለማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። አቶ አራርሳ አያይዘው የመንግስት ተቋማት የሚያገናኛቸውን ስትራቴጂክ ጉዳዮች ለማከናወን የሚፈጠር መዋቅራዊ አደረጃጀት በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል ለተፈፃሚነቱ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል። በልደታ ክ/ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ በበኩላቸው እንዳሉት ተቋማት በቅንጅት እንዲሰሩ፣ ተሻጋሪ የሆኑ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን፣ የተወሳሰቡ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የዜጎች ፍላጎት በማሟላት ውጤታማነታቸውን ለማሻሻል ማስፈፀሚያ ማንዋሉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የአገልግሎት አሰጣጥና የህብረተሰቡን ተሣትፎ በማሻሻል የዜጎች አመኔታ በመንግስት ተቋማት ላይ እንዲጨምር ያደርጋል በማለት አቶ አሰፋ አክለው ገልፀዋል። የማስፈፀሚያ ማንዋል ሰነዱን ያቀረቡት የልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ ሲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግ፣ አንድ ወጥ አሰራርን በማዘጋጀት በመንግስት ተቋማት ትብብርን በማጠናከር የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። የውይይቱ ተሳታፊ በበኩላቸው ይህ ተቋማዊ ቅንጅት አሰራር በርካታ የተወሳሰቡ ችግሮችን እንደሚፈታ አንስተው ለማንዋሉ ተፈፃሚነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች