image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ያለበት ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል ምልከታ ተካሄደ

ጥቅምት 15, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር "በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" ብሎ በጀመረው ፕሮግራም መሠረት የአገልግሎት አሰጣጡ ያለበትን ደረጃ ለመገምገም በተለያዩ ወረዳዎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል። የክ/ከተማውፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ፣ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ፣ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በልደታ ከ/ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በወረዳዎች ያለው የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን በምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል። ተገልጋዮች በበኩላቸው ፈጣን ፣ግልፅና ችግር ፈች አገልግሎት እያገኘን ነው ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ግልፀኝነትን የፈጠረው የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ በርካታ ችግራችን እየተፈታ ነው ሲሉ ተገልጋዮች ጨምረው ገልፀዋል። የአገልግለት ዕለትን ለተገልጋይ ብቻ በማዋል የህዝብ እሮሮን ለመቀነስ ብሎም በተገልጋዮች የሚነሱ አንገብጋቢ የሆኑ ጥያቄዎችን በአግባቡ አድምጦ የመመለስ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች