image
image
image
image
image

"ህዝብን ማዳመጥ እና ለህዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ መስጠት ለነገ የምናሻግረው ሳይሆን ዛሬ የምንፈፅመው ተግባር ነው"ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

ህዳር 14, 2017
በልደታ ክ/ከተማ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ ቀጥሏል። በተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተገልጋዮችን ሲያስተናግዱ ያገኘናቸው የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት በተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለአደሩ የህዝብ ጥያቄዎች ሳይቀር ፈጣንና ችግር ፈች ምላሽ እየሰጠን ተጠቃሚነትን እያረጋገጥን ነው ብለው አስተዳደሩ ያደሩ የህዝብ ጥያቄዎችን ከመመለስ ባሻገር የኢንሼቲቭ ስራዎችን በማከናወን የላቀ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የልደታን ከፍታን ለማረጋገጥ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማሻገር የለብንም ብለን 24/7 እየሰራን እንገኛለን ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ህዝብን ማዳመጥ እና ለህዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ መስጠት ለነገ የምናሻግረው ሳይሆን ዛሬ የምንፈፅመው ጉዳያችን ነው በማለት ተናግረዋል። በየደረጃው ያለ አመራርና ባለሙያ ተግባራትን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ መርሁ አድርጎ እንዲሰራ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠርን ነው ያሉት ወ/ሮ ልዕልቲ በትጋትና በቁርጠኝነት ከሰራን የልደታን ከፍታ በአጠረ ጊዜ እናረጋግጣለን ሲሉ ተናግረዋል። የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደተናገሩት በተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ማህበረሰቡ የሚያቀርባቸውን ጥያቄዎች በማያዳግም መልኩ ምላሽ እየሰጠን ነው ብለው በዚህም እርካታን ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች