image
image
image
image
image

ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮችን ጥያቄ እንመልሳለን። - ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

ታህሳስ 11, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የባለ ጉዳይ ቀንን ምክንያት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ምልከታ ተደርጓል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ፣ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንዲሁም ሌሎች የተቋም ሀላፊዎች በተገኙበት የተገልጋይ ቀንን ምክንያት በማድረግ የተቀናጀ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። ተገልጋዮችን ተቀብለው እያነጋገሩ ያገኝናቸው የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንዳሉት ቀልጣፍና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮችን ጥያቄ እየመለስን እንገኛለን ብለዋል። ማገልገል ክብር ነው ያሉት ወ/ሮ ልዕልቲ በተለይ የክፍለ ከተማውን ማህበረሰብ ማገልገል ከክብር በላይ ክብር ነው ብለዋል። በክፍለ ከተማው በባለ ጉዳይ ቀን አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ እንዲሁም ማህበረሰቡን ለማርካት እና የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የሚያስችል የተቋማት የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች