image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የኢትዮጲያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዛር ተከፈተ።

ህዳር 16, 2017
በክፍለ ከተማው "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጲያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓልን አስመልክቶ በሜክሲኮ አካባቢ ባዛር ተከፍቷል። ባዛሩን የከፈቱት የልደታ ክ/ከተማ የመልካም አስተዳደርና ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ እንደተናገሩት በባዛሩ የተዘጋጀው ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አስመልክቶ መሆኑን ገልፀው በባዛሩም ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ ቀርበዋል ሲሉ ገልፀዋል። መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ ከቅዳሜና እሁድ ገብያዎች ባለፈ በተለያዩ ሁነቶች ባዛሮችን እያዘጋጀ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ በላይነህ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ማህበረሰቡ ወደ ባዛሩ በመምጣት የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምትም አቶ በላይነህ ጥሪ አቅርበዋል። የክ/ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ሂሩት በቀለ በበኩላቸው ባዛሩ ለተከታታይ 5 ቀናት እንደሚቆይ ገልፀው ማህበረሰቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምትም ጥሪ አስተላልፈዋል። በባዛሩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረባቸውንም ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች