image
image
image
image
image

ማህበረሰብ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አስተዳደሩና ተቋሙ በልዩ ትኩረት በመስራት ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ።

ህዳር 4, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ መልካም አስተዳደር የቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ለጉለሌ ክፍለ ከተማ መልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ልምድ አካፈለ። በጽ/ቤቱ የተሰሩ ለልምድ ተሞክሮ የሚሆኑ ሪፖርት በማቅረብ የተሰሩ ስራዎችና ሰነዶችን ማየት ችለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ መልካም አስተዳደር የቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በልምድ ልውውጡ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት በአስተዳደሩ በሚሰጠው አገልግሎቶች ላይ የነበረው ምልልስ ከማህበረሰብ ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት በማድረግና መግባባት ላይ ተደርሶ ምልልሱን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል ። የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን ከብሎክ ጀምሮ በመለየት በየደረጃው መፍታት መቻሉን የገለፁት አቶ በላይነህ አያይዘው በአስተዳደሩ ምቹ የስራ ቦታ መፍጠርና ተቋሙን በሰው ሀይል ማሟላት መቻሉ ለሚሰጠው አገልግሎት ወሳኝ መሆኑ ገልፀዋል። ተገልጋዮች ወደ አስተዳደሩ ግቢ ለመገልገል ሲመጡ አስተዳደሩን ውብና ለስራ ምቹ ለአገልግሎት ማራኪ የማድረግ ስራዎች መሠራት በቻሉን አቶ በላይነህ ገልፀዋል። በጽ/ቤቱ አዲሱ ቅንጅታዊ አሰራር ወደ ተግባር በማስገባት የተቀላጠፈ የስራ አፈፃፀም እንዲኖር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከተቋሟት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አቶ በላይነህ ገልፀዋል። በአስተዳደሩ ከ58 በላይ በራስ አቅም የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት መጀመርና ማስጨረስ ማህበረሰብን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በመጨረሻም ልምድ ልውውጡ ያደረጉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ አቻ ተቋም በጽ/ቤት የተሰሩ ተግባራት የተሻለና የማህበረሰብን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ነው በማለት የተደረጉ ወይይቶች የተገልጋዮችን እንግልት የቀነሰበት አግባብ የተሻለ ልምድ እንደወሰዱ አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች