image
image
image
image
image

በአንድ ማዕከል ለተገልጋዮች የሚሰጠው አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መስከረም 10, 2017
የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የባለጉዳይ ቀንን በማስመልከት እየተሰጠ በሚገኘው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ ምልከታ ባደረገበት ወቅት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ፣የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪባን ጨምሮ ሌሎች የተቋማት ሀላፊዎች ባለጉዳዮችን ሲያስተናግዱ መመልከት ተችሏል። የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን አግኝቶ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ፈጣን ምላሽ እያገኙበት እንደሚገኝ ገልፀዋል። አስተያየታቸውን የሰጡን ተገልጋዮች እንደገለፁት በተለይም ሁሉም የስራ ሀላፊዎች በአንድ ማዕከል በመገኘት እየሰጡት ያሉት አገልግሎቶች ግልፅነትንና ታማኝነትን የሚፈጥር ላነሷቸው ጥያቄዎች አጥጋቢ ማብራሪያና ምላሽ እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ባለጉዳዮችን በአንድ ማእከል እንዲሁም የፅህፈት ቤት ኃላፊዎች በየቢሯቸው በመገኘት እያስተናገዱ ይገኛሉ

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች