image
image
image
image
image

"በአስተዳደሩ እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ በተቋማት ላይ እምነት እንድናሳድር አስችሏል" ተገልጋዮች

ህዳር 5, 2017
"የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ዕርካታን እያረጋገጠ ነው" አስተዳደሩ በልደታ ክ/ከተማ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ፈች በሆነ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ፈች ሆኖ ቀጥሏል ብለው አገልግሎት አሰጣጡ አስተዳደሩ የተገልጋዮችን ዕርካታ ለማሳደግ እንዲችልም ትልቅ አቅም ሆኖታል ሲሉ ገልፀዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለውም አገልግሎት አሰጣጣችን ፈጣን ቀልጣፋና ፍትሀዊ ከመሆን ባለፈ የተገልጋዮችን ምልልስ የሚቀንስና ችግር ፈች እንዲሆን ተደርጓል ብለው ለዚህም ተገልጋዮች ምስክርነት እየሰጡ ነው በማለት ተናግረዋል። የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደገለፁት በተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ የበርካታ ዜጎች የመልካም አስተዳደር ችግር ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል ብለው ተግባሩ በተቀናጀ እና በተደራጀ መንገድ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል። አቶ አራርሳ አክለውም የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ፈች ሆኖ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል። ተገልጋዮች በበኩላቸው በተቀናጀ የአንድ መዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎቻች ፈጣን ምላሽ እያገኙ ነው በዚህም በተቋማት ላይ እምነት እንድናሳድር አስችሎናል ሲሉ ገልፀዋል። ፈጣን ግልፅና ፍትሀዊ አገልግሎት በማግኘታችን ደስተኞች ነን ያሉት ተገልጋዮች ለዚህም አስተዳደሩን አመስግነዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች