image
image
image
image
image

"በተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ምልልስን መቀነስ የቻለ ግልፅና ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠን ነው"ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

ጥቅምት 14, 2017
በልደታ ክ/ከተማ እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መግለጫ የሰጡት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት አገልግሎት አሰጣጣችን የተገልጋይ ምልልስን የሚቀንስ፣ ግልፅና ተደራሽ እንዲሆን ቀዳሚ አጀንዳችን አድርገን እየሰራን ነው ብለው በዚህም ባለፍት ጊዚያት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ ችለናል ሲሉ ገልፀዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለውም አገልግሎት አሰጣጣችን ከቢሮ አልፎ እስከ ብሎክ ተደራሽ የሚሆንበትን ስርዓት ዘርግተናል ብለው በዚህም የበርካታ ነዋሪዎች ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ ችለናል በማለት ተናግረዋል። አገልግሎት አሰጣጣችን ምላሽ ሰጭ እንዲሆን ተደርጓል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በአመራሩና በባለሙያው ዘንድ ቅድሚያ ለተገልጋይ የሚለውን መርህ አስርፀን እርካታን የማሳደግ ስራ እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች